Fana: At a Speed of Life!

ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለአንባቢዎች ያበረከቱትና አንጋፋው ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የእድሜ ልክ የክብር አባል የነበሩት ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማህበሩን ጠቅሶ ዘግቧል።

የደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ የቀብር ስነ ስርአት የፊታችን ረቡዕ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.