Fana: At a Speed of Life!

የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን ተመቶ ሲወድቅ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል የቀረጸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን መታ የጣለችውን የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን ተንቀሳቃሽ ምስል የቀረጸውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች።

የኢራን ብሄራዊ አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሃይል ግለበሱን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን፥ ግለሰቡ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር የተያያዘ ክስ ሊመሰረትበት ይችላል ነው የተባለው።

መኖሪያውን ለንደን ያደረገ ኢራናዊ ጋዜጠኛ ደግሞ የሃገሪቱ ባለስልጣናት የተሳሳተ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን በትዊተር ገጹ አስፍሯል።

ኢራን እስካሁን ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎችን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር አውላለች።

176 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው የዩክሬን የመንገደኞች አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ተመቶ መውደቁ ይታወሳል።

በወቅቱ ምዕራባውያን አውሮፕላኑ ተመቶ መውደቁን ሲገልጹ ኢራን አስተባብላ ነበር።

ይሁን እንጅ አውሮፕላኑ ተመቶ መውደቁን ያሳያል የተባለው ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች መለቀቁን ተከትሎ ኢራን “በስህተት” መታ መጣሏን ማመኗ አይዘነጋም።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም የሃገሬው ዜጎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.