Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

8ኛ መደበኛ 6ኛ የስራ ዘመን 6ኛ ዓመት ስብሰባውን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ነው እያካሄደ የሚገኘው።

በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በስብሰባው ላይም የክልሉ የኮንስትራከሽን ባለስልጣን፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የስምንት ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

እንዲሁም የክልሉ መንግስት የልማት ድርጅቶችና የማዕድን ሀብት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ የወደፊት አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ነው የተነገረው።

የኦሮሚያ ክልል የ10 ዓመት የብልፅግና ጉዞ እቅድ በስብሰባው ላይ ቀርቦ እንደሚፅድቅም ይጠበቃል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.