Fana: At a Speed of Life!

ሳምንቱ ምዕራባውያን ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተጨባጭ ለማወቅ ፍላጎት ያሳዩበትና በተግባርም እንቅስቃሴ ያደረጉበት – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ  በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የህዳሴ ግድብ ድርድር ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫቸው  የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሆኑት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ የተመራ ከፍተኛ ልዑካንን ማነጋገራቸውን ገልፀዋል።

በዚህ ወቅት አቶ ደመቀ  ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ 86 በመቶ ውሃ የሚታበረክት አገር መሆኗዋንና  60 በመቶ የሚሆኑት ዜጎቿ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለማግኘት በጨለማ ውስጥ የሚኖር መሆኑን አስረድተዋል።

ግድቡ በጨለማ የሚኖር ህዝቧን ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ ፕሮጄክት መሆኑን  በማስረዳትም የአባይ ውሃን በፍትሃዊና እኩልነት መርህ  ለልማት ማዋል የኢትዮጵያ ህጋዊና ሉዓላዊ መብት መሆኑን እና ኢትዮጵያ ታችኞቹን የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን የመጉዳት ምንም ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል።

በሱዳንና በግብጽ በኩል የሚነሱ  ስጋቶች ለመፍታት የሶስትዮሽ ድርድር  ሲካሄድ መቆየቱን በማስታወስ፤ የሚነሱ ጉዳዮች በድርድር መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ኢትዮጵያ  በቁርጠኝነት ሳታቋርጥ ሲትሳተፍ እንደቆየች  አብራርተዋል፡፡

በግድቡ የውሃ ሙሌት የግንባታው አንድ አካል መሆኑን በማስረዳት ከአሜሪካ ጋር በትብበር ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን  አቶ ደመቀ ማረጋገጣቸውን በመግለጫው ላይ አንስተዋል።

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ በሰጡት መግለጫም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የአለም አቀፍ አካላትን ባካተተ ሁኔታ በገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲደረግ ዝግጅቶች ተደርገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር ተፈፀመ የተባለውን የሰበአዊ መብት ጥሰት ለማጣራት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ያለፈው ሳምንት ምዕራባውያኑ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተጨባጭ ለማወቅ ፍላጎት ያሳዩበትና በተግባርም እንቅስቃሴ ያደረጉበት መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በአጠቃላይ በሀገሪቱ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመገንዘብ የቻሉበች ነው ብለዋል።

በአዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.