Fana: At a Speed of Life!

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።

ውጤቱን ለማየት http://result.neaea.gov.et የሚለውን አድርሻ መጠቀም እንደሚቻል ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ሀገር አቀፍ ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55 ነጥብ 7 በመቶዎቹ ከ350 በላይ ማምጣታቸውን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሪ አስታውቀዋል

የፈተና ውጤቱ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 702 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት እንዳመጡ ተገልጿል።

የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም 669 ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል ።

ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑን  ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.