Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማስፋፊያ ተርሚናል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማስፋፊያ ተርሚናል ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ያለውን ለውጥ ለመጎብኘት በመቻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡
በባዮ ሴፍቲ እና ባዮ ሴኪዩሪቲ ላይ ባተኮረ ዘመናዊ የአቪዬሽን እየተገነባ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ግንባታው አዲስ ተርሚናል፣ የክብር እንግዳ መቀበያ ሳሎን፣ የቢዝነስ ላውንጅ እና ሌሎች ተቋማትን መያዙንም ገልጸዋል፡፡
የቪአይፒ ተርሚናሉ ከአየር መንገዱ የማስፋፋያ ስራዎች መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.