Fana: At a Speed of Life!

በግል ትምህርት ቤቶች የኮቪድ መከላከል መመሪያ መተግበሩን ለመመልከት ድንገተኛ ቅኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በመገኘት የትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ መመልከቱን አስታወቀ።

ምልከታ ከተካሄደባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል ሳንፎርድ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና አሜሪካ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ይገኙበታል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ በጉብኝታቸው ትምህርት ቤቶቹ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል እያከናወኑት ያለውን ተግባር የተመለከቱ ሲሆን በትምህርት ቤቶቹ አስተዳደርም እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን መመሪያ በአግባቡ መተግበራቸውን በጉብኝታቸው ወቅት መመልከታቸውን ገልፀዋል።

ሌሎች ትምህርት ቤቶችም የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል እና ትምህርት ቤቶች ዳግም እንዳይዘጉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሊያደርጉ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል።

በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ቤቶች ድንገተኛ ቅኝት በማድረግ ትምህርት ቤቶች ሚኒስቴሩ ያወጣውን መመሪያ እየተገበሩ መሆኑን እንደሚያጣራ እና መመሪያውን ባልተገበሩ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወሰድ መገለጹን ከሚስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.