Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕከት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕከት አስተላለፉ፡፡

አቶ ደመቀ “ለመላው የሃገራችን ህዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን አብሮ ደስ አለን” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ደማቅ ታሪክ ላስመዘገቡ የብሔራዊ ቡድኑ አባላትና አመራሮች በሚገባ አኩራታችሁናል ሲሉ ማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ለዚህ አኩሪ ድል ስላበቃችሁን በሃገራችን መንግስትና በብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት ስም የተሰማኝን ልዩ ክብር በመግለፅ፤ ታላቅ አድናቆቴ እና ምስጋናዬ ይድረሳችሁ” ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.