Fana: At a Speed of Life!

ለጢያ መካነ ቅርስ የትክል ድንጋይ እድሳትና እንክብካቤ ስራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ለጢያ መካነ ቅርስ የትክል ድንጋይ እድሳትና እንክብካቤ ስራ መከናወኑ ተገለፀ።

የጢያ መካነ ቅርስ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘና  በቅርስነት ተመዝግቦ  የሚገኝ ቢሆንም የጎብኝዎች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆኑ ቅርሱን የማስተዋወቁ ተግባር ሊጎለብት ይገባል ተብሏል።

በጢያ ከሚገኙ ተክል ድንጋዮች በተጨማሪ በሶዶ ወረዳ  ከ100 በላይ ተክል ድንጋዮች መኖራቸውን የወረዳው ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አዳነ ተሰማ የገለፁ ሲሆን ማሰባሰብና የበለጠ ማልማት ቢቻል የተሻለ ገቢን ማግኘት አንደሚያስችል ተናግረዋል።

የጢያ ተክል ድንጋይን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ቢሆንም ከዚህ ቀደም ቦታው በተፈለገው ደረጃ ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን  ይገልፃሉ።

በ2012 ዓ.ም በውስጡ የሚኙትን ቅርሶች የመጠገንና ከጉዳት ለማዳን ሶስት ሚለየን ብር በጀት በመያዝ ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስራ ተቋርጦ እንደነበረ ነው የተነገረው።

በ2013 ዓ.ም ዳግም ስራውን በማስጀመርና 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጭ በማድረግ የተለያዩ ስራዎች መከናወኑን እና ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

ከፌዴራል ባህል ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው ገንዘቡም ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን መገኘቱን አስታውቀዋል።

በእቅዱ መሰረትም አሲዳማ የሆነውን የአካባቢውን አፈር ቅርሱ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጠርጎና ቆርጦ የማንሳትና የመቀየር ስራ በማከናወን ቅርሱን ከጉዳት መታደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በተጨማሪም የጥገና ፣ የጎርፍ ማፋሰሻዎችን የማበጀት ፣ የማስዋብና ሌሎች መሠል ስራዎች  እንደተናከናወኑ ተናግረዋል ።

ቅርሱን ለብዙ መቶ አመታቶች ጠብቆ ያቆየው የአካባቢውን ማህበረሰብ ያመሰገኑት ሀላፊው   ይህም መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅርሱ በዩኔስኮ ከተመዘገበ 41 አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም የልማት ስራዎች ሳይሰሩ መቆየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ያነሳሉ።

በቅርቡ የተከናወነው ተግባር ቅርሱን ከጉዳት የሚታደግ በመሆኑ ትልቅ ደስታን ፈጥሮልናል ሲሉ ተናግረዋል።

የጢያ መካነ ቅርስ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘና ለረጅም ግዚያቶች በአለም ቅርስነት ተመዝግቦ ያለ በመሆኑ በዚያው መጠን እንዲጎበኝ ለማድረግ የማስተዋወቁ ተግባር ሊጎለብት ይገባል ብለዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.