Fana: At a Speed of Life!

ሃገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን ምዘና መርሀ-ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሃገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን ምዘና መርሀ-ግብር ተጀመረ።

በንቅናቄው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ፤ትምህርት የአንድ ሃገር ታሪክ ነው ለዚህም በክርስታና እና እስልምና እምነቶችም ስለትምህርት ሲያስተምሩ እና ሲሰብኩ መቆየታቸው የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

እነዚህ ተቋማት አሁንም ቢሆን ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት ያላቸው አስተዋፅኦ ጎልቶ የሚታይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቄስ ትምህርት ቤት በመክፈት እና በማስፋፋት፣ የእስልምና ሃይማኖት መድረሳን በመክፈት እና በማስፋፋት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሊመሰገኑ ይገባልም ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዘመናዊ ትምህርትን ለማስፋት እና ለማሳደግ ላለፉት 70 አመታት በርካታ ስራዎች ቢሰሩም ከሚያስፈልገው የትምህርት ምጥጥን አንፃር  አሁንም ክፍተት አለ ብለዋል።

ይህ አዲሱ የትምህርት ብርሃን ምዘና ንቅናቄ ወጣቶች እና ጎልማሶች በእውቀት የበለፀጉ በማድረግ መሃይምነትን መቀነስ ያስችላልም ነው የተባለው።

ፕሮግራሙ የሃገሪቱን ወጣቶች እና ጎልማሶች የማንበብ፣ የመፃፍ እና የማስላት ክህሎት በመመዘን በሚያገኙት ውጤት መሰረት እውቅና መስጠት የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል።

በምዘናውም አጥጋቢ ውጤት ያስመዘገቡ ወጣቶች እና ጎልማሶችን እንደየፍላጎቶቻቸው የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላልም ነው የተባለው።

በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣የክልል የስራ ሃላፊዎች  እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በይስማው አደራውና በፋሲካው ታደሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.