Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት እየተወሰደ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስትቅንጅት እየተወሰደ መሆኑን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት በማውገዝ የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ገልጸዋል፡፡

በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “ዓለማችን በወረርሽኝ ተጨንቃ መፍትሔ በምትፈልግበት በዚህ ሰዓት፣ ሆን ብለው በሰዎች ላይ መከራና ስቃይ የሚጨምሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በምንፈልጋት ኢትዮጵያ ውስጥ ስፍራ የላቸውም” ብለዋል።

“ጠላቶቻችን በውስጥና በውጭ ተደራጅተው ንጽሐን ዜጎቻችንን በመግደል የጀመርነውን ጉዞ ለማሸማቀቅና ከመንገዳችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው። መሥዋዕትነት እየከፈልንም ቢሆን የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክረን ጉዟችንን እንቀጥላለንም” ነው ያሉት።

“መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ጥፋት ኃይሎች ወጥመድ ላለመውደቅ በማስተዋል እየተጓዘ፤ በእንደዚህ ዓይነትጉዳዮች ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እና እንደዚህ ዓይነት ግድያዎች ፈጽመው እንዲቆሙ በትብብር ልንሠራ ይገባልም” ብለዋል በመልዕክታቸው።

ኢትዮጵያ በመሥዋዕትነት የቆመች፤ በመሥዋዕትነት የምትቀጥል ሀገር ናት። በትብብርና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያን ጠላቶች ደግመው እንዳይነሡ አድርገን ማጥፋት አለብን።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.