Fana: At a Speed of Life!

በአቶ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ ሁዋጃያን ቀላል አምራች ኢንዱስትሪ መንደርን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ ሁዋጃያን ቀላል አምራች ኢንዱስትሪ መንደርን ጎበኘ፡፡
ጉብኝቱ የኢንዱስትሪ መንደሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዳይገባ ያደረጉ ችግሮችን መቅረፍ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሁዋጃያን ቀላል አምራች ኢንዱስትሪ መንደር 200 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ፣ ለ7 ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ፣ 540 የሚሆኑ ወጣቶችን ቻይና በመውሰድ ስለጫማ የቴክኖሎጅ ውጤቶች እውቀት እንዲያገኙ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ለ1 ሺህ ዜጎች የጤና ኢንሹራንስ መግዛቱ፣ 6 ሚሊየን ብር ለህዳሴ ግድብ በመለገስና ሁለት ቦታዎች ላይ የመጠጥ ውኃ ገንብቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ በማስረከብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ የኢንዱስትሪ መንደር ነውም ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው ይህ የኢንዱስትሪ መንደር በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን እያመረተ ያለውን 15 ሺህ ጥንድ ጫማዎችን ወደ 35 ሺህ የማምረት አቅም በማሳደግ ለ50 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል መባሉን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.