Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም በመጪው ክረምት የሚተከል ከአንድ ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአርሶ አደሩ ዘንድ እየተለመደ የመጣውን የቡና ልማት ለማስፋፋት በመጭው ክረምት የሚተከል ከአንድ ሚሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የመስኖ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ አህመድ እንደገለጹት፤ አርሶ አደሩ ከሰብል በተጓዳኝ ቡና በማልማት የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተጀመረው የቡና ልማት 1 ሺህ 500 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ 1 ሺህ 170 ሄክታር ማሳ መሸፈኑን ተናግረዋል።

የተገኘውን ልምድ በማስፋት በመጪው ክረምት የሚተከል 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የቡና ችግኙ 350 ሄክታር አዲስ መሬት ላይ የሚተከል መሆኑን አመላክተዋል።

የተዘጋጁት የቡና ችግኞች በሽታ ተቋቁመው በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ምርት መስጠት የሚችሉ ዝርያዎች መሆናቸውን አቶ ሀብታሙ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.