Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ዴልተር የቤልጂየምን የ2020/21 የቁንጅና ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ዴልተር የቤልጂየምን የ2020/21 የቁንጅና ውድድር አሸነፈች፡፡

የ23 ዓመቷ ቅድስት የጸጉር ስራ ባለሙያ ስትሆን ቤልጂየም ውስጥ ናዝሬት ከተባለ ምስራቃዊ ፍላንደርስ መምጣቷ ተገልጿል፡፡

ስነስርዓቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያለታዳሚ ነው የተካሄደው ተብሏል፡፡

ቅድስት ትውልዷ አዲስ አበባ ሲሆን በስምንት ዓመቷ እናቷን አጥታለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ ወደ ማሳደጊያ መግባቷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከአስረኛ ዓመቷ ጀምሮ ደግሞ ቤልጂየማውያን ጥንዶች በማደጎ እንዳሳደጓት በቤልጂየም ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.