Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሰብአዊ ዕርዳታ ሰጠች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች 46 ሜትሪክ ቶን ምግብና የህክምና አቅርቦቶችን ድጋፍ አደረገች፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር መሃመድ ሳሌም አል ራሺዲ “የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችና ኢትዮጵያ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡
ይህ ድጋፍም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለወንድማማች እና ወዳጃዊ ህዝቦች ሰብአዊና የልማት ዕርዳታ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው መመሪያዎች አካል ናቸው” ብለዋል ፡፡
ሃገሪቱ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊና የልማት ሁኔታን ለመደገፍ እየሰራች መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡
በተጨማሪም ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ለሌሎች ዓለም ሃገራት ድጋፍ እንደምታደርግ ማስታወቃቸውን የኢሚሬትስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከዓለም የምግብ ፕሮግራም እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ 5 ሚሊየን ዶላር ቃል ገብቷል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.