Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የፖሊዮ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል።
የክትባት ዘመቻውን ያስጀመሩት በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና የጤና ማበልፀግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዲ ፋራህ በክልሉ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ህፃናት እንደሚከተቡ ተናግረዋል።
የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሙስጠፋ መሀሙድ በበኩላቸው ክትባቱ በከተማው በሚገኙ 20 ቀበሌዎችና በከተማዋ ዙሪያ ባሉ 10 ቀበሌዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው ህብረተሰቡ ልጆችን በወቅቱ እንዲያስከትብ ጥሪ አቅርበዋል።
ክትባቱ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ደርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.