Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ፖሊሶች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለ12ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 800 የፖሊስ አባላት በዛሬው እለት አስመርቋል ፡፡
በምረቃ ስነ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ “ዜጎች ሰላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሶማሌ ክልል መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል”ብለዋል፡፡
ፖሊስ በፖሊሳዊ ሙያቸው ዜጎችን እንዲያገለግሉና ሰላምን እንዲጠብቁ ትልቅ ሀላፊነት አለበትም”ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ፡፡
የክልሉን ሰላም የበለጠ ለማጠናከርም ሌሎች 1 ሺህ ምልምል ፖሊሶች በቀጣይ እንደሚመረቁና በሁሉም የፀጥታ መዋቅሩ ላይ በቁሳቁስና በሰው ሀይል ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሽ በበኩላቸው በሶማሌ ክልል ያለውን አስተማማኝ ሰላም ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀው በፀጥታ ሀይሉ ላይ በተሰራው ለውጥ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.