Fana: At a Speed of Life!

በሳምንቱ ከተመረመሩ ሰዎች ውስጥ በሽታው የመገኘት ምጣኔ በአማካይ 25 በመቶ ሆኗል- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ  የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላልና ለመቆጣጠር በሚያስችሉ የትኩረት ጉዳደዮች ዙርያ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ህዝባችንን ከዚህ የከፋ ወረርሽኝ ማዳን የጋራ ኃላፊነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ የሆኑት ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ÷ በእምነት ተቋማት የተጀመሩት የጥንቃቄ እርምጃዎች አበረታች ቢሆንም አሁንም የተጀመሩትን ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል

በዚህም ሀይማኖታዊ አገልግሎቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ፣የእጅ ንጽህና  እንዲሁም ከቫይረሱ መተላለፊያ ባህሪይ አንጻር ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች መገልገያ ቁሳቁሶችን መዋዋስ ሳያስፈልግ  እንዲከናወኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ ባሳለፍነው ሳምንት ከተመረመሩ ሰዎች ውስጥ በሽታው የመገኘት ምጣኔ ሳምንታዊ አማካይ 25 በመቶ ከመሆኑም ባለፈ  በሽታው የተገኘባቸው ሰዎችም ቁጥር ከ200 ሺህ  ተሻግሯል ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ሊያ ንግግር ይህን አስከፊ ወረርሽኝ ለመግታት ለባለድርሻ አካላት በቀረበው ጥሪ መሰረት እጅግ አበረታች እንቅስቃሴዎች በብዙ ባለድርሻ አካላት መጀመሩን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ህዝቡን በማስተማር፣ በማሳሰብ እና በሃይማኖት ስነስርዓት ወቅት አስፈላጊውን መከላከያ ዘዴዎችን ለማስተግበር በገቡት ቃል መሰረት ወዲያዉኑ ስራ ላይ ማዋል መጀመራቸውን እና ህብረተሰቡም እያሳየ ላለው የተግባር ተባባሪነት እጅጉን አመስግነው ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ዶክተር ሊያ   በመልዕክታቸውም ሁላችንም በዕለት ዕለት እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ ጥንቃቄ ካደረግንና ግዴታችንን ከተወጣን እየተስፋፋ ያለውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በጋራ መግታትና መቀነስ ስለሚቻል ሁላችንም ዳግም ትኩረት ለኮቪድ 19 ምላሽ በመስጠት ህዝባችንን ከከፋ ጉዳት መታደግ የጋራ ኃላፊነት ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.