Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይቀጥላል – ዶክተር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚደረግ አስታወቁ፡፡

ድርድሩ በአዲሷ የህብረቱ ሊቀመንበር በሆነችው በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፓብሊክ አወያይነት ነው የሚካሄደው፡፡

ድርድሩ የሚካሄደው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የውሃ ሚኒስትሮች ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት መሆኑን ዶክተር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል፡፡

የህበረቱ ባለሙያዎች፣ ታዛቢዎች እና የሦስቱ ሃገራት ባለሙያዎች በድርድሩ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡

ሚኒስትሩ አባይ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብት መሆኑን ጠቅሰው የህዳሴ ግድቡ ትልቅ የኃይል ምንጭ የሚሰጥ

መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

የኃይል አቅርቦቱን ከማሳደግ በተጨማሪም ልማትን የሚደግፍ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቱን ጉልህ ጉዳት ሳያስከትል በመርህ ላይ የተመሰረት ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ የሆነ አቋም እንዳላት ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.