Fana: At a Speed of Life!

የአንድ አገር ዋነኛና ቀዳሚ የልማት ተዋናይ መንግስት ቢሆንም የሲቪል ማህበረሰቡም ከፍተኛ ድርሻ አለው -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የሴቶች ወር መርሃ ግብር ማጠቃለያ የሆነዉ በሴቶች ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበራትን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተካፈሉበት ስብሰባ ላይ ተገኝተዉ ባሉባቸዉ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዝደንቷ የአንድ አገር ዋነኛና ቀዳሚ የልማት ተዋናይ መንግስት ቢሆንም የሲቪል ማህበረሰቡም ከፍተኛና ወደ ጎን ሊባል የማየቻል ሚና እንዳለዉ ግልጽ ነዉ ብለዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ከዚህ በፊት በጠሩት የሲቪል ማህበራት ስብሰባ ላይ የሲቪል ማህበራት ቅንጅትና ትስስር ሀገራዊ የልማት ዕቅዶችን ከማሳካት ረገድ ያለዉን ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው÷ ማህበራቱ በዚህ ረገድ እንዲደራጁ ማሳሰባቸዉ ይታወሳል፡፡

በስብሰባዉ ፍጻሜም ይህንን ጥረት የሚያስተባብር አካል ተቋቁሟል፡፡

የሴቶችን ጉዳይ የበላይ ባለቤትና አስተባበሪ የሆነ ድርጅት አስፈላጊነት ላይ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ዝግጅት መጀመሩን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.