Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ የራሱን ጉዳይ በራሱ መወሰን የሚችልበት የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ወጣቱ የራሱን ጉዳይ በራሱ መወሰን የሚችልበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት ውይይት ተካሄደ፡፡

በዚሁ ወቅት የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ኢትዮጲያ የአፍሪካ ሀገራት መዲና እንደመሆንዋ መጠን መሰራት ያለበትን ስራ አልሰራንም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ በ2004 ዓ.ም የወጣቶች ፖሊሲ ሲጸድቅ የወጣቶች ካውንስል በፌደራል ደረጃና በክልል ደረጃ እንደሚሰራ መካተቱን አስታውሰዋል፡፡

እስካሁን ምንም ዓይነት ስራዎች አልተሰሩም ነገርግን አሁንም ጊዜው አልረፈደም የወጣቶችን ካውንስል መስርተን ትልቅ ለውጦችን ማምጣት እንችላለን ብለዋል፡፡

ወጣቱ የራሱን ጉዳይ በራሱ መወሰን የሚችልበት ዕድል ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት አላማውንና አስፈላጊነቱን በተመለከተ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የወጣቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማቲያስ አሰፋ ናቸው፡፡

ሚኒስትሯ ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ፣ረዳት ፕሮፌሰር ታምራት እና የወጣቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማቲያስ አሰፋ የቀረበው ጽሁፍ አስፈላጊነቱን እና ለወደፊቱም ሊካተቱ የሚችሉ ሀሳቦችን በግብዓት መልኩ በመውሰድ የወጣቶችን ካውንስል ለመመስረት የሚያስችል ሁኔታዎች ላይ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ሀገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስልን ለመመስረት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች ፣የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች እና ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ጋር የውይይት መድረክ መካሄዱንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.