Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ 3ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 3ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በሸራተን አዲስ ተከበረ፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሃላፊነት የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአመራራቸው ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች ለመዘከር ያለመ መርሃ ግብር ነው እተካሄደው።

ሚኒስትሮችና የፌደራል እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት ስነስርአት፣ የሶስት አመቱን የለውጥ ጉዞ የሚዳስስ መነሻ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።

በዚህ ወቅትም ከለውጡ በኋላ የታዩ መልካም ጅምሮች ተነስተዋል፣ ዛሬም የብዙዎች ጥያቄ የሆነው የሰላም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠውም ተጠይቋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ታሪካዊ ቀን ወደ ሃላፊነት እንደመምጣታቸው የለውጡ አመራር ለፕሮጀክቱ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ እንደ ስኬት ተነስቷል።

ያልጎለበተ የዴሞክራሲ ባህል፣ ብሄርና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች፣ ያልተቋጨው የህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የታጠቁ ሃይሎች ያልተገታ እንቅስቃሴ የለውጡ ስጋትና ፈተና ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡

እድሎቹ እንዳሉ ሆነው ፈተናዎቹን በድል ለመወጣት ቀጣይ ስራ እንደሚጠይቅና ርብርቡ ሁሉን አቀፍ መሆን እንዳለበትም ተነስቷል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.