Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻነት ሰነድ በተቋማቱ ነጻነቶች ሳይሸራረፉ ለማስተግበር የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነጻነቶች ሳይሸራረፉ ለማስተግበር የተቋማዊ ነጻነት ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ማስገባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ::

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻነት ማዕቀፍ ሰነድ ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

የምክክር መድረኩን የከፈቱት  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አሁን ያለው ሀገራዊ የለውጥ ቁመና ባለፉት ጊዜያት በአዋጅ የተሰጡ ነገር ግን በትግበራ ወቅት ያልተሳኩ ተግባራት ለመፈጸም የሚያስችል በመሆኑ ይህንን ማሳካት እንዲቻል ክፍተትን አስተካከሎና አርሞ መጓዝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌም፤ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በሃላፊነት ካልጻፉ ፣ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ካልቻሉ፣ ካልተመራመሩ እና በሪፎርም ካልተመሩ  የሃሳብ ድርቀት ፈተና ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሚዘጋጀው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻነት ማዕቀፍ  ሰነድ የተቋማትን ሁለንተናዊ  ነጻነቶች ሳይሸራረፉ ለማስተግበር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ እንዲሆን እና ዘርፉን ወደፊት ለማስኬድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰነድ ዝግጅቱን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂክ ማዕከል ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ሀብታሙ ተካ በበኩላቸው፤ ማዕቀፉ የተቋማት አስተዳደራዊ፣ የፋይናንስ፣ የሰው ሀብትና የአካዳሚክ ነጻነት ጉዳዮች በአግባቡ ለመምራት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እሙየ ቢተው ማዕቀፉ ከዚህ በፊት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ቁልፍ ሚና ስለሚኖረው ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማዕቀፉ ዝግጅት ግብአት መስጠት እንደለባቸው መግለፃቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የማዕቀፉን  አስፈላጊነት በመጥቀስ ሊስተካከሉና ሊታረሙ ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.