Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ከአንድ ግለሰብ ከ115 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ 115 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖት መያዙን የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር እስከዳር ካሳዬ ገልፀዋል።
በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 5 ሰዓት አካባቢ ጌትነት መኩሪያ የተባለ ተጠርጣሪ በደሴ ከተማ ቀበሌ 6 በሚገኝ ለማረፊያ ከተከራየበት አልጋ ቤት ውስጥ ያስቀመጠው 115 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖት በአልጋ ቤቱ ባለቤት ጠቋሚነትና በኅብረተሰቡ ትብብር መያዙን ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪው በተከራየው አልጋ ቤት ካስቀመጠው ሀሰተኛ የብር ኖት በተጨማሪ በእጁ ይዞ እየተገበያየ እያለ በቁጥጥር ስር እንደዋለም ነው የገለፁት፡፡
የተያዘው ሀሰተኛ የብር ኖት 109 ሺህ 200 ብር ባለ 200 የብር ኖት እና 6 ሺህ 100 ብር ባለ 100 የብር ኖት መሆኑን አብመድ ዘግቧል።
ህብረተሰቡም ሲገበያይ በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ኢንስፔክተር እስከዳር መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.