Fana: At a Speed of Life!

የሮቤ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 90 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በ774 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለዉ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 90 በመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡
ፓርኩ በ10 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በቡልቡላ ከተማ እየተገነባ ላለዉ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግብዓቶችን እንዲያቀርብ ታልሞ እየተገነባ ያለ ነው፡፡
የሮቤ ከተማ ካንቲባ አቶ ገዛኝ ደጀኔ ፓርኩ የግብርና ግብዓቶች ላይ እሴት እንዲጨምሩና የዞኑ አርሶ አደሮች እንዲጠቀሙ እንደሚያስችል ገልፀው ለገበያ የሚቀርበዉ የግብርና ምርትም በጥሬ ከመሸጥ የሚያስቀር አላማን ያነገበ ነዉ ብለዋል፡
ፓርኩ በምርት ግብይት ወቅት በመካከል እየገባ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚጎዳ ደላላን በማስቀረትም የዋጋ ንረትን የመቀንስ ሚና እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡
ፓርኩ በመንግስት በጀት እየተገነባ ያለ ሲሆን ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ እንደሆነም ታውቋል፡፡
በለማ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.