Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በኤግዚም ባንክ በኩል ባደረገው የ30 ሚሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት የተገዙ የህክምና መሳሪያዎችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍቢሲ)የኢትዮጵያ መንግስት በኤግዚም ባንክ በኩል ባደረገው የ30 ሚሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት የተገዙ የህክምና መሳሪያዎችን መረከቡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት የህክምና መሳሪያዎቹ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዙ የኢትዮጵያ መንግስት ከኮሪያ መንግስት በኤግዚም ባንክ በኩል ባደረገው የ30 ሚሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት የተገዙ ናቸው፡፡
የህክምና መሳሪያዎቹም የኮቪድ19 መመርመሪያ መሳሪያ፣ የመተንፈሻ ድጋፍ ሰ
መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የጽኑ ህሙማን ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ናቸው ተብሏል፡፡
ለዚህም ሚኒስትሯ የኮሪያ መንግስት የኮቪድ ወረሽኝን በመዋጋት ሂደት ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.