Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከስፖርት ቤተሰብ ተወካዮች ጋር በከተማዋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከስፖርት ቤተሰብ ተወካዮች ጋር በከተማዋ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

የስፖርት ቤተሰቡ  ሰላም እና ወንድማማችነትን ከማጎልበት ባለፈ በኮቪድ ወረርሽን ወቅት ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች እያበረከቱት ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ እና የሚበረታታ መሆኑን በውይይቱ ገልጸዋል።

በከተማዋ ያሉ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ወደ አጎራባች የክልል ከተሞች በመሄድ ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለወንድማማችነት እና ለአብሮነት ያለውን አስተዋጽኦ በተግባር እየታየ ነው ብለዋል፡፡

በነገው ዕለትም ወደ አምቦ ከተማ በማቅናት ህዝቦችን በስፖርት ለማስተሳሰር ለሚጓዙ ልዑካን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለረጅም ዓመታት የወጣቶች ጥያቄ የነበሩ የጃንሜዳን ጨምሮ የፈረንሳይ ጨፌ ሜዳ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እንዲካሄድ የከተማ አስተዳደሩ ያደረገው ተግባር ይበል የሚያሰኝ መሆኑን የስፖርት ተወካዮቹ ገልጸዋል።

በጋራ ውይይቱ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቡና፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለቦች የደጋፊዎች ማህበር፣ የስፖርት ለሰላም ማህበር እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰብ ተወካዮች መሳተፋቸውን ከአዲስአበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.