Fana: At a Speed of Life!

“ብዙዎቹ ችግሮቻችን ከመደመር እሴቶች መላላት የሚመነጩ ናቸው”- መምህር እና ሃያሲ መሠረት አበጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስነ-ፅሁፍ መምህር እና ሃያሲ መሠረት አበጀ “ብዙዎቹ ችግሮቻችን ከመደመር እሴቶች መላላት የሚመነጩ ናቸው” አሉ፡፡

መምህሩ ይህንን ያሉት “የመደመር መንገድ” የመፅሐፍ ዳሰሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው በዚህ የመፅሐፍ ዳሰሳ መድረክ የስነ-ፅሁፍ መምህር እና ሃያሲ መሠረት አበጀ፣ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ዶክተር ጠና ዳዎ እና ዶክተር ጌታነህ መሃሪ በመፅሃፉ ይዘት ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን እያቀረቡ ነው፡፡

መድረኩ መፅሐፉን ከስነ-ፅሁፋዊ ይዘቱ፣ ከፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም እና ከፍልስፍና አውድ አንፃር የሚመለከት ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛ የስልጣ ዘመን መፅሐፍ የሆነው “የመደመር መንገድ” ብዙዎቹ ችግሮቻችን ከመደመር እሴቶች መላላት የሚመነጩ ናቸው ብሎ እንደሚያምን ገምጋሚዎቹ ገልፀዋል፡፡

ሆኖም የመፅሐፉ ደራሲ “ኢትዮጵያ የቱንም ያህል ብትንገዳገድ ከጀመረችው መንገድ እና ከብልፅግና ጉዞዋ የሚገታት የለም” የሚል ፅኑ አቋም እንዳላቸው ሃያሲዎቹ ተናግረዋል፡፡

መፅሐፉ መደመር የለውጥ መርህ፤ የለውጥ ጥሪ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን የጋራ ራዕይ እና መፍጠር የምንፈልጋትን ሃገር ማወቅ ይጠበቅብናል  የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ እሳቤ በሁሉም የስነ-ፅሁፍ መሰረታዊ ዓላባውያን አስውቦ ያቀረበ ነው ብለዋል፡፡

በሶዶ ለማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.