Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን 16ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የሰመራ ጉምሩክ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መከፈት የሀገሪቱ የገቢና የወጭ ንግድ እንዲሳለጥ ከማድረጉ በተጨማሪ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ያሳድጋል ብለዋል፡፡

የንግድ ስርዓቱ በጤናማ መንገድ እንዲጓዝ ብሎም ለአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠር የሚያበረክተው አስተዋጽዖ የጎላ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ለደንበኞች ፈጣን አገልግሎት መስጠት፣ በህግና በአሰራር ማገልገል፣ ኮንትሮባንድንና ህገወጥ ንግድን መከላከል በቀጣይ በትኩረት መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች እንደሆኑም   አስገንዝበዋል፡፡

የጅቡቲ፣ የጋላፊ፣ የታጁራ እና የአሰብ ወደቦች ለአፋር ክልል ቅርብ በመሆናቸው ይንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአካባቢውን የልማት ጸጋዎች የመለየት፣ ወደሀብት ምንጭ የመቀየር  ብሎም የስራ አጥነትን ችግር መቅረፍ እንደሚገባም ማስረዳታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.