Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልልን በተመለከተ በቡድን ሰባት አባል ሃገራት የወጣው መግለጫ እውነታን ያላገናዘበ ነው-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልልን አስመልክቶ በቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የወጣው መግለጫ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ጉልህ እርምጃዎችን ያላገናዘበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ መንግስት በክልሉ የተከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አመላክቷል፡፡
ሆኖም ከትናንት በስቲያ በቡድን ሰባት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሰጠው ማግለጫ ይህን ከግንዛቤ ሊያስገባ አልቻለም ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡
መንግስት የሚዲያ ተቋማትን ጭምሮ ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለተገደብ እንቅስቃሴ ፈቃድ ቢሰጥም ከአለም አቀፉ ማሕበረሰብ እየቀረበ ያለው እርዳታ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመልክቷል፡፡
በክልሉ ተፈጽሟል ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትም አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ምርመራ እነዲያደርጉ ፈቃድ የተሰጣቸው ሲሆን ሥራቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስፍሯል፡፡
እንዲሁም መንግስት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ተረጂዎች እርዳታ ማቅረቡን ያስታወሰው መግለጫው ከዚህ ውስጥ ከአለም አቀፍ ማሕበረሰብ የተገኘው የዕርዳት መጠን ከአንድ ሶስተኛ በታች መሆኑን ገልጿል፡፡
በመሆኑም በክልሉ ያለው ችግር ሙሉ በሙሉና በወቅቱ እንዲቀረፍ ከተፈለገ በቂ የእርዳታ አቅርቦትን ማሰባሰበ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ መግለጫው አመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል የኤርትራ ጦር ከድንበር አከባቢ ለቆ መውጣት መጀመሩንና የአትዮጵያ መከላከያ ኃይል መረከቡን በመግለጫው ተገልጿል፡፡
በክልሉ ሙሉ በሙሉ የመንግስት መዋቅርን ለመዘርጋትም ጥረት እየተደረገ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.