Fana: At a Speed of Life!

ምርጫውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማከናወን በየደረጃው ያሉ የክልል አመራሮች በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማከናወን በየደረጃው ያሉ የክልል አመራሮች በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ የፌዴራል የምርጫ ጸጥታ አስፈጻሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

ኮሚቴው እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት የጎላ ችግር ሳያጋጥመው ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከናወኑንም ገልጿል።

የፌዴራል የምርጫ ጸጥታ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተለያዩ  የመንግስት ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ የተቋቋመ ሲሆን፤ ዋነኛ ዓላማውም ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናወን ነው።

ኮሚቴው ከክልልና ከተማ መስተዳደር ተወካዮች ጋር በመሆን እስካሁን ያለውን የምርጫ ጸጥታ አፈጻጸም ገምግሟል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት ሰላማዊ መሆኑን ገልጸዋል።

እጀባ በማድረግ የምርጫ ቁሳቁሶችን ያለምንም ችግር ማጓጓዝ መቻሉንና በምርጫ ጣቢያዎች ከደረሱ በኋላም ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ነገር ግን በውስን አካባቢዎች የምርጫ እጩዎችን ተገቢ ባለሆነ መልኩ ማንገላታትን ጨምሮ ጥቃቅን የሆኑና ቶሎ መታረም የሚችሉ ችግሮች መከሰታቸውን ገልጸዋል።

የመከላከያ ሚኒስትርና የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ቀነዓ ያደታ በበኩላቸው የምርጫ ጽህፈት ቤት ከፍቶ ወደ ስራ ማስገባት፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማጓጓዝና የእጩዎች ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.