Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ይካሄዳል።

ጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀጣይነት ላለው የሃገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚዳሰስበት እና ከኢጋድ አባል ሃገራት የተውጣጡ ዩንቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት መሆኑን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።

ጉባኤ ከነገ  መጋቢት 27 ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል።

የኢጋድ ዩንቨርሲቲዎች የሚታደሙበት ይህ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ የሚካሄደው ሲሆን ከኢጋድ አባል ሃገራት የተውጣጡ 20 ዩኒቨርሲቲዎች ይካፈሉበታል።

ጉባኤው በአባል ሃገራቱ ላይ እየተስተዋሉ ስለሚገኙ የዜጎች ስደት እና መፈናቀል የሚመክር ሲሆን የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ይከፍቱታል ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.