Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ ለአቅመ ደካሞች፣ ወጣቶችና ሴቶች መኖሪያ ቤቶችና የመስሪያ ቦታ ሼዶችን አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 85 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤቶች እና 770 ሴቶች እና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 166 የመስሪያ ቦታ ሼዶችን አስረከበ።

በቁልፍ ርክክብ መርሐ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፤ የከተማዋ ሀብት በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ለህዝቡ መድረስ ይገባዋል፤ለዚህም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የተጀመረው የልማት እና የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ሁሉም መተባበር እና መተጋገዝ ይገባዋል ሲሉ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አሳስበዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የመንግስት ቤቶችን በማስለቀቅ  85 ያህሉን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ማስተላለፍ መቻላቸውን ገልጸዋል ።

እንዲሁም ለረጅም አመታት ተደራጅተው የመስሪያ ቦታ ሼድ ለመውሰድ ሲጠባበቁ ለቆዩ በ181 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 770 ሴቶች እና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 166 የመስሪያ ቦታ በዕጣ መተላለፊን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.