Fana: At a Speed of Life!

ታዋቂው ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ።

አቤል ተስፋዬ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በረሃብ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

ዘ ዊኬንድ አሁን ላይም በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የገለፀው በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም በድምፃዊው የተደረገው ድጋፍ ወሳኝ ነው ብሏል።

ድጋፉ የአለም ምግብ ፕሮግራም በመጪው ስድስት ወራት የአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.