Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን በበረዶ ናዳ የ77 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፓኪስታን በተከሰተ የበረዶ ናዳ የ77 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በሰሜናዊ ፓኪስታን በተከሰተው ናዳ ከሞቱት በተጨማሪም 94 ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው።

ለተከታታይ ቀናት በአካባቢው የጣለው በረዶና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ለበረዶ ናዳው ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የተነገረው።

ኒለም ሸለቆ አካባቢ በደረሰው ናዳ በርካታ መኖሪያ ቤቶች በበረዶ መቀበራቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገልጸዋል።

በአካባቢው ካለው የአየር ሁኔታ አንጻር የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላልም ነው የተባለው።

የጦር ሄሊኮፕተሮችም ከአደጋው በህይዎት የተረፉትን እና የተጎዱ ሰዎችን ወደ መጠለያ ስፍራዎች እያጓጓዙ ነው።

በበረዶ ናዳው ሳቢያ በአካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ የኤሌክትሪክ አቅርቦትና የስልክ አገለግሎት መቋረጡም ተነግሯል።

በሌላ በኩል በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ ባሎችስታን ግዛት በዚህ ሳምንት በጣለ ከባድ ዝናብ እና በበረዶ ምክንያት፥ በ48 ሰዓታት ውስጥ 16 ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።

ምንጭ፡- ሲ.ኤን.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.