Fana: At a Speed of Life!

የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት ጋር አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ኮሚሽንና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት በኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ በተቋም ለውጥ እና አቅም ግንባታ ላይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የፕላንና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋና የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት ተወካይ አቶ አክሊሉ ፍቅረሥላሴ ተፈራርመዋል።
የእቅድ እና የፖሊሲ ንድፎችን በጋራ የመሥራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ከድህነት ጋር ያለውን ተዛማጅነት እና ተጽዕኖውን መገምገም ላይ የአቅም ግንባታ ማጠናከር፣ በጋራ በሚደረጉ ምርምሮች የሚገኙ ውጤቶችን ለመጋራት የሚያግዝ አውደጥናት፣ ሴሚናር እና ሲምፖዚየም በጋራ ማዘጋጀት የስምምነቱ አካል ናቸው፡፡
እንዲሁም ከአየር ንብረት እና የኢኮኖሚ እድገት ጋር በተገናኘ የወደፊቱን አዳዲስ ባለሙያዎች በሥልጠና አቅማቸውን ለማሳደግ የምርምር ማዕከል መገንባት እና ዓለም አቀፋዊም ሆነ ሃገራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር በእውቀት ሽግግር እና በስትራቴጂ ላይ የሚደረጉ ግንኙነቶችን መደገፍም በስምመነቱ ተካቷል፡፡
የፕላንና ልማት ኮሚሽን በኢኮኖሚ እድገት እና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ በምርምር የታገዘ ውሳኔ ለማድረግ፣ በተቀመጠለት ማዕቀፍ ለማቀድ የዳታቤዝ አቅሙን ለማበልጸግ እንዲሁም አቅሙን ለማሳደግ ጠንካራ ተሞክሮ ካላቸው ተቋማት ልምድ ለመጋራት ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ኢንስቲቲዩቱ በኢትዮጵያ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ ለሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር አስተዋጽኦ ለማድረግ ከፍ ያለ ፍላጎት እንዳለው መገለጹን ከፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.