Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከተመድ ዋና ፀሀፊ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ልዩ ተወካይና በሱዳን የተመድ የተቀናጀ የሽግግር ድጋፍ ተልዕኮ ሃላፊ ቮልከር ፐርተስ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ወቅትም አምባሳደሩ የኢትዮ ሱዳንን የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና ድርድር ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያን ምክንያታዊ አቋም አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከሰብአዊ ድጋፍና የሚዲያ ተቋማት በክልሉ ገብተው እንዲንቀሳቀሱ ከማድረግ አኳያ የታዩ ለውጦችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.