Fana: At a Speed of Life!

በልዩ ልዩ ኃላፊነትና በመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂነት ያገለገሉት ብፁዕ  አቡነ ጢሞቴዎስ አረፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በልዩልዩ ኃላፊነትና በመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂነት ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አረፉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ዛሬ ተገልጿል፡፡

ከአባታቸው ባራምባራስ ተስፋ ተክሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ታህሣ ኃይሉ በ1930 ዓ.ም ግንቦት ወር በትግራይ ክልል ብዘት ወረዳ የተወለዱት ብፁዕነታቸው÷ በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት መግለጹን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅትን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.