Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን እያደረጉት ካለው ውይይት ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጽም አረጋ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሶስቱ ሃገራት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በተለያዩ ዙሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።

በዚህም በግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፥ በቅርቡ የተደረገው አራተኛ ዙር ስብሰባ ግብጽ በግድቡ የውሃ አሞላል ላይ ይዛ በቀረበችው አዲስ ሃሳብ ምክንያት ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የአራተኛውን ዙር ስብባ መጠናቀቅ ተከትሎም እስካሁን ባደረጓቸው ድርድሮች የደረሱባቸውን ነጥቦች የሚገመግሙበት ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ እያደረጉ ይገኛል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.