Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ወራት በወርቅ ገበያ ከ20 እስከ 29 በመቶ የዋጋ ጭማሪ በመደረጉ የተሻለ ገቢ ተገኝቷል – የማዕድን እና የነዳጅ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በህገወጥ መንገድ (በጥቁር ገበያ) የሚሸጠውን የወርቅ ግብይት ለማስቀረት ባለፉት ወራት ከ 20 እስከ 29 በመቶ የዋጋ ጭማሪ በመደረጉ የተሻለ ገቢ ማግኘቱን የማዕድን እና የነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የማዕድን ግብይት ስራዎች ብቃት ማረጋግጥ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ጫላ ዲዳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፤ መንግስት ባደርገው የማሻሽያ ስራ ከቡና ቀጥሎ ከፍ ያለ ገቢ ማስገኝቱን ገልፀዋል።

ይህም ብሔራዊ ባንክ እና ማዕድን ሚኒስቴር በተሻለ ሁኔታ በጋራ በመስራት በዚህ ዓመት የተሻለ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል ።

በዚህም 404 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል ።

በዚህም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከወርቅ ግብይት በዚህ ዓመት የተሻለ ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።

ወርቅ እና ሌሎች ማዕድናትን ለማምረት ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ችግር ባልተሟላበት አካባቢ በመሆኑ በዘርፉ የሚስተዋለውን ህገወጥ የማዕድን ግብይት ለመከላከል ሁሉም ማህበረሰብ ርብርብ ማድርግ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.