Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል በ50 ሚሊየን ብር ወጪ ደረጃውን የጠበቀ የወጣት ማዕከል ሊያስገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል በ50 ሚሊየን ብር ወጪ ደረጃውን የጠበቀ የወጣት ማዕከል ሊያስገነባ ነው፡፡
ማዕከሉ በክልሉ ሸንኮር ወረዳ የሚገነባ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በተለይ በአሁኑ ወቅት ወጣቱን ወደ ልማትና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ማስገባትና ሀገራዊ ለውጡን ፍሬያማ እንዲሆን ማድረግ፣ወጣቶች በመልካም አስተሳሰብ፣ በክህሎትና እውቀት ታንፀው ራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህ አንፃርም የወጣቶች ማዕከላትን በመገንባትና ግብዓት በማሟላት ውጤታማ ስራ ማከናወን ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም ይህ የወጣት ማዕከል ሲጠናቀቅም በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም በበኩላቸው የሚገነባው ማዕከል የወጣቶችን ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ማለታቸውን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.