Fana: At a Speed of Life!

የግልና የመንግስት ትብብር ሲጠናከር የአገር እድገትን  ያግዛል- ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍና የመንግስት ትብብር ሲጠናከር የአገር እድገትን ለማገዝ ይረዳል ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።

የሲቪል ማሕበረሰብ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍና መንግስትን ለማስተሳሰር ያለመ ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዳሉት÷ የአንድ አገር እድገት ሊመጣ የሚችለው በሁሉም ትብብር ነው።

በተለይም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍና የሲቪል ማሕበረሰብ አጋርነትና ትብብር ለኢትዮጵያ እድገትና ለውጥ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

መንግስትም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የዘርፎችን ትብብር የሚያጠናክሩ የሕጎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎችን አድርጓል ነው ያሉት።

በዚህም ባለፈው አንድ አመት በቂ ነው ባይባልም የተወሰኑ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

ይህን መሰል ትብብርና አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ አቃቤ ዶክተር ጌዲዮን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.