Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ 2 ሺህ 54 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ8 ሺህ 190 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሺህ 54 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በቫይረሱ 25 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 25 ደርሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም አሁን ላይ 850 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

934 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.