Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች  የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰዓትና የጋዜጦች የአምድ ድልድል የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰዓትና የጋዜጦች የአምድ ድልድል የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ተካሄደ።

የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ ድልድሉ ዛሬ መውጣቱን ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከነገ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዘጋጅነት የተካሄደ ነው።

ድልድሉ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ52 መገናኛ ብዙሃን ማለትም በ21 ሬዲዮ ጣቢያዎች ፣ በ23 ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና በ8 ጋዜጦች  መከናወኑ ተነግሯል።

በራዲዮ 620 ሰዓታት ፣ በቴሌቪዥን 425 ሰዓታት እና በጋዜጣ በ625 አምዶች የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በስነ ስርዓቱ ላይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህም መሰረት ከነገ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት  23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በእነዚህ መገናኛ ብዘሃን የምርጫ ቅስቀሳቸውን ያደርጋሉ።

በዘቢብ ተኽላይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.