Fana: At a Speed of Life!

በእነ ስብሃት ነጋ ላይ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተያዘው ቀጠሮ ምስክር ሳይሰማ ታገደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በእነ ስብሃት ነጋ ላይ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተየዘው ቀጠሮ ምስክር ሳይሰማ ታግዷል፡፡

እነስብሃት ነጋ በዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር አሰማም ሂደትን በተመለከተ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው ዕለት በእነስብሃት ነጋ ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ችሎት ተሰይሞ ነበር፡፡

ይሁንና ችሎቱ የምስክር አሰማሙ ላይ እግድ በመጣሉ እግዱ እስከሚነሳ ድረስ መዝገቡን ዘግቻለሁ ብሏል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ግን ይግባኝ ለተባለበት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬውኑ ክርክር እናድርግበት በማለት ያመለከተ ቢሆንም፤ ይግባኙን የሚመለከተው ችሎት ዳኛ በህመም ምክንያት ባለመሟላታቸው እንዲሁም ዐቃቤ ህግ ማመልከቻ ያቀረበበት ችሎት በስራ ጫና ምክንያት መመልከት አልችም በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ለሚያዚያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በይግባኙ ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.