Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ለኢጋድ አባል ሀገራት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለኢጋድ አባል ሀገራት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

ከቁሳቁሶቹ መካከል 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰርጂካል ማስክ፣ 24 አምቡላንስ እና ተንቀሳቃሽ መመርመሪያ ላቦራቶሪ እንደሁም የኮቪድ19 መመርመሪያዎች ይገኙበታል።

ከዚህም መካከል 500 ሺህ የሚሆን ሰርጂካል ማስክ፣ 100 ሺህ ሰርጂካል ካፕስ፣ 100 ሺህ ኤን 95 ማስክ፣ 25 ሺህ ሰዎችን የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ የሚበቃ የምርመራ ኪት፣ አንድ አድቫንስድ አምቡላንስ እንዲሁም ኮቪድ19 ለመመርመር የሚረዳ አንድ ተንቀሳቀሽ ላቦራቶሪ ለኢትዮጵያ እንደሚደርሳት ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የኮቪድ19 ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው ድጋፉ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አሁን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ከሚያደርጉ አራት ሰዎች ውስጥ አንዱ በኮቪድ19 እየታመመ መሆኑን በመግለጽም ኅብረተሰቡም ይህን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ በቀጠናው ላሉ ሀገራት እና በአካባቢው ላሉ ሀገራት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚጠቅም ሲሆን በሀገር ውስጥ ለተፈናቀሉም ሆነ በስደት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ሰዎች ተደራሽ የሚደረግ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

በድጋፉ በአብዛኛው መተማ አካባቢ፣ ጋምቤላ ኩምሩክ እንዲሁም ሞያሌ አካባቢ ያሉ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.