Fana: At a Speed of Life!

ቤተክርስቲያኗ ከ7 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የእርዳታ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከ7 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የእርዳታ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርጋለች፡፡
ቤተክርስቲያኗ 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቃለች፡፡

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በተከሰቱ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ እና የእለት ደራሽ ምግብ በማቅረብ ላይ ትገኛለችም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን በኩል በበጀት ዓመቱ ትኩረት የተደረገባቸው ዘርፎች ጤና፣ ትምህርት፣ የምግብ ዋስትና፣ የሴቶችና ህጻናት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ከስደት ተመላሾችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከልማት ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን 40 ሚሊየን ብር በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ለምግብ፣ ቁሳቁስ፣ ለመድሃኒት እና ለተፈናቃይ ወገኖች የዕለት ደራሽ ምግብ እንዲውል ተመድቧል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መድባ በ180 ፕሮጀክቶች ከ6 ሚሊየን የሚበልጡ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጓን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.