Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍላጎት እውን የሚሆንበት አንዱ ዘርፍ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ እና ቴሌኮሙዩኒኬሽን የኢትዮጵያ የብልጽግና እና የኢኮኖሚ ዕድገት ፍላጎት እውን የሚሆንበት አንዱ ዘርፍ መሆኑን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ቴሌኮም ሪቪው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ እና ቴሌኮሙዩኒኬሽን ብልጽግና እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሚረዳ አንዱ ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዘዋወር ሂደቱ የአዲስ ዘመን ጅማሮ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፥ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን በማሰብ የሚከናወን መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አያይዘውም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ፋና ወጊ ለመሆን ፍላጎት ያላት ሀገር መሆኗንም ነው የተናገሩት፡፡

ይህን እቅድ ለማሳካትም በ10 ዓመቱ የብልጽግና መሪ ዕቅድ ውስጥ መካተቱንም አስረድተዋል፡፡

ቴሌኮምን ወደ ግሉ ዘርፍ የማዘዋወር ሂደትም የሀገሪቱን የዲጂታል አጀንዳ እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ይህ ሂደት አቅም ያላቸውን ተቋማት ዕውቀት ለመጠቀም ትልቅ እድል ይፈጥራልም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.