Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ በሕብረቱ በኩል በጽኑ የሚታመን መርህ መሆኑን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው ከተመረጡት ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ በቅርቡ በኪንሻሳ የተካሄደው የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማገኘት እንዳለባቸው በማመንም በአፍሪካ ሕብረት አስተባበሪነት የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥል በኢትዮጵያ በኩል ጽኑ እምነት ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩልም በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በመሻሻል ላይ መሆኑን ለምክትል ሊቀመንበሯ አብራርተዋል።
ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋን በበኩላቸው ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ በአፍሪካ ሕብረቱ በኩል በጽኑ የሚታመን መርህ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ በዚህ አንጻር ለያዘችው አቋም ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት ያጋጠመውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሕብረቱ ሰራተኞች ክትባት አንዲደርሳቸው በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ድጋፍ አንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል።
አቶ ደመቀ ለአፍሪካ ሕብረት ሰራተኞች ተገቢው የክትባት አገልግሎት እንዲደርሳቸው ማደረጉ ተገቢ መሆኑ ገልጸው፣ ለተፈጻሚነቱም ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ መናገራቸውታውቋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ደመቀ መኮንን ዶክተር ሞኒክ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይ በሚኖራቸው የስራ እንቅስቃሴ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.