Fana: At a Speed of Life!

የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ሰነድ ለሕዝብ ሊሠራጭ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያዘጋጀው የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ሰነድ በሚቀጥለው ሳምንት ለሕዝብ እንደሚሰራጭ ተገለፀ፡፡
በቀጣዩ ሳምንት ለሕዝብ እንዲደርስ የተሰናዳው የዚሁ የልማት እቅድ ቅጅ በዋነኝነት በፕላን እና ልማት ኮሚሽን ድረ ገጽ እንደሚለቀቅ ታውቋል፡፡
በተጨማሪም በኮሚሽኑ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን በሌላ በኩል በመጽሐፍ መልክ የተሰናዳው ሰነድ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በህትመት ሒደት ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የህትመት ሒደቱ ሲጠናቀቅ ደግሞ በተመሳሳይ ለሕዝብ የሚሠራጭ ይሆናል ነው የተባለው፡፡
በኢትዮጵያ በቀደሙ ዓመታት የልማት ዕቅድ ትግበራ ክፍተቶችን እንዲሁም የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ከግምት በማስገባት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳለጥ እንዲረዳ የተዘጋጀ ዕቅድ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
የተቀመጠውን ኢትየጵያን “አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት” የማድረግ ሀገራዊ የልማት ራዕይ ለማሳካት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የተዘጋጀው ይህ የልማት ዕቅድ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.